1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ይሁንታ ያገኘው የኮቪድ 19 ክትባት

ሐሙስ፣ ኅዳር 24 2013

ብሪታንያ ከምዕራባውያን ሃገራት በቀዳሚነት ለኮቪድ 19 ክትባት ይሁንታ በመስጠት ዜጎቿን ለመከተብ መዘጋጀቷን አሳውቃለች። የአውሮጳ ሕብረት አባል ሃገራት ግን የጋራ ውሳኔ እየተጠባበቁ ነው።

https://p.dw.com/p/3mBqp
Biontech Covid-19 Impfstoff
ምስል NurPhoto/picture alliance

«ብሪታንያ ቀዳሚዋ የምዕራብ ሀገር ሆናለች»

ብሪታንያ ከምዕራባውያን ሃገራት በቀዳሚነት ለኮቪድ 19 ክትባት ይሁንታ በመስጠት ዜጎቿን ለመከተብ መዘጋጀቷን አሳውቃለች። ክትባቱን የጀርመኑ ባዮንቴክና የአሜሪካው ፋይዘር የተባሉት የመድኃኒት ኩባንያዎች ቤልጂየምላይ በማምረት እንዲያቀርቡ ነው ውሉ። የብሪታንያ የጤና ሚኒስትር ክትባቱ ከሚቀጥለው ሳምንት መጀመሪያ አንስቶ ለአዛውንቶችና ለሚንከባከቧቸው ሠራተኞች እንዲሁም ለህክምና ባለሙያዎች እንደሚሰጥ ነው የተናገሩት። የአውሮጳ ሕብረት አባል ሃገራት ግን የጋራ ውሳኔ እየተጠባበቁ ነው። 

ገበያው ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ