ያልሰመረው የሆረዬ ፕሮጀክት
ረቡዕ፣ ነሐሴ 4 2003ማስታወቂያ
ገበሬዎቹ ለዶቼቬለ በሰጡት አስተያየት ከላይ የወረደ መመሪያ ነው ተብሎ የተጫነባቸው የውሐ ማቆር ሥራ ጉልበት ከማባከን በስተቀር አንድም ጥቅም እንዳላስገኘላቸው ተናግረዋል ። ይልቁንም ለዚሁ ሥራ ተብሎ የታደለውን ላስቲክ ለታሰበለት የውሐ ማቆሪያ ሳይሆን ለቤት ክዳንና ሌሎች ግልጋሎቶች ጥቅም ላይ ማዋላቸውንም አስታውቀዋል ። ሥራው ውጤታማ ያልሆነበት ምክንያት በቂ ጥናት ተደርጎ ባለመጀመሩ መሆኑን በወቅቱ በዚህ ስራ ላይ የተካፈለ አንድ የእርሻ ልማት ሰራተኛ ተናግሯል ። ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ከመቀሌ ዝርዝር ዘገባ አለው ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ሂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሰ