ዩናይትድ ስቴትስ ጥሪና የኤርትራ መልስ
ሐሙስ፣ ሐምሌ 14 2003ማስታወቂያ
የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪቃ ጉዳዮች ምክትል ሚኒስትር ጆኒ ካርሰን ማክሰኞ እንደተናገሩት ኤርትራ ሁኔታውን በግልፅ ማሳወቋ ሊደርስ የሚችል አስከፊ አደጋን ለመቋቋም ይረዳል ። ኤርትራ በበኩሏ በሀገርዋ የረሃብና የድርቅ አደጋ እንዳልተከሰተ ፣ ቢከሰት እንኳን ችግሩን ለመቋቋም የሚያስችል በቂ አቅም አለን ስትል አስታውቃለች ። ዶቼቬለ ያነጋገራቸው የኤርትራ ፕሬዝዳንት የአቶ ኢሳያስ አፈወርቂ የፖለቲካ አማካሪ አቶ የማነ ገብረ አብ በኤርትራ እስካሁን የሚያሰጋ ሁኔታ የለም ብለዋል ። አሜሪካን ለኤርትራ ህዝብ ካሰበችም የሚጠበቅባት የኤርትራን የልማት እቅድ መደግፍና በኤርትራ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ ማንሳት የመሳሰሉትን እርምጃዎች መውሰድ መሆኑን አቶ የማነ ተናግረዋል ። ዝርዝሩን የዋሽንግተን ዲሲው ዘጋቢያችን አበበ ፈለቀ ልኮልናል ።
አበበ ፈለቀ
ሂሩት መለሰ
ተክሌ የኋላ