1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዩናይትድ ስቴትስ ስለኢትዮጵያ ወቅታዊ ኹኔታ

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 12 2014

ዩናይትድስቴትስ በኢትዮጵያው የሚካሄደውን ጦርነት ለማስቆም እንዲቻል ዲኘሎማሲያዊ ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥል አስታወቀች። የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ ኔድ ኘራይስ ትናንት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት ተዓማኒነት ያለውና ሁሉንም ያሳተፈ ብሄራዊ ውይይት እንዲጀምር ጥሪ አቅርበዋል።

https://p.dw.com/p/44eet
US | Ned Price Sprecher des Außenministeriums
ምስል Kevin Lamarque/Pool/AP/picture alliance

ለሁሉን አቀፍ ብሔራዊ ውይይት ጥሪ አድርጋለች

ዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያ የሚካሄደውን ጦርነት ለማስቆም እንዲቻል ዲኘሎማሲያዊ ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥል ዐስታወቀች። የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ ኔድ ኘራይስ ትናንት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የኢትዮጵያ መንግሥት ተዓማኒነት ያለውና ሁሉንም ያሳተፈ ብሄራዊ ውይይት እንዲጀምር ጥሪ አቅርበዋል። መንግሥት በጦርነቱ የህወሃት ኃይሎችን ድል አድርጎ ከእየ አካባቢዎቹ ማስወጣቱን ሲገልጥ፤ ሕወሓት ከአማራ እና ከአፋር ክልል የወጣሁት ለ«ሠላም» ነው ይላል። ዩናይትድ ስቴትስ ጦርነቱ በአስቸኳይ እንዲገታ መጠየቋን እንደምትገፋበት ዐስታውቃለች። ዩናይትድ ስቴትስ ሁሉን አቀፍ ብሔራዊ ውይይት ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲደረግም መንግሥትን መጠየቋን ገልጣለች። 

ታሪኩ ኃይሉ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ኂሩት መለሰ