1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
መገናኛ ብዙኃንዓለም አቀፍ

የDW ዲዛይን : ለምን በመጠኑ መቀየር አስፈለገን?

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 1 2016

አካታችነት እና ተደራሽነት ለወደፊቱ የድርጅታችንን መገለጫ ለማጎልበት ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ። ወደፊት ይዘቶቻችን ይበልጥ ያለምንም እንቅፋት የሚቀርቡ ይሆናል።

https://p.dw.com/p/4a0Ix
የDW ድረ ገጽ እና መተግበሪያ ላይ የበለጠ የንድፍ (ዲዛይን) ማሻሻያ እየተደረገ ነው
የDW ድረ ገጽ እና መተግበሪያ ላይ የበለጠ የንድፍ (ዲዛይን) ማሻሻያ እየተደረገ ነውምስል DW

በአዲስ እና የተሻለ ገጽታ፤ እንዲሁም ለተጠቃሚ በሚስብ መልኩ ለማቅረብ የንድፍ ወይም የዲዛይን ክፍላችን ለወራት ሢሠራ ቆይቷል። አንዳንድ አዳዲስ የተደረጉ ለውጦችን ልግለጽላችሁ። 
አካታችነት እና ተደራሽነት ለወደፊቱ የድርጅታችንን መገለጫ ለማጎልበት ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ።  ወደፊት ይዘቶቻችን ይበልጥ ያለምንም እንቅፋት የሚቀርቡ ይሆናል።
ድረ-ገጾቻችን እና መተግበሪያዎቻችን በቴክኒክ በኩል ለተጠቃሚዎች የተሻሉ ሆነው ተመቻችተዋል። 
ለተሻሻለው ግልጽ አቀራረብ ምሥጋና ይግባው እና አሁን የፈለጉትን መረጃ በፍጥነት ማግኘት ይችላሉ። ንባብዎን የበለጠ ምቹ ለማድረግ የአጻጻፍ ስልቱንም እየቀየርን ነው። ዝርዝሩ ላይ የተደረጉት ማስተካከያዎች እና ከበስተጀርባ ያሉ ገፅታዎች በግልጽ ማንነታችንን በመለየት የአስተማማኝ መረጃዎቻች ምንጭነታችንን ያጠናክራሉ።
መለያ ቀለማችን እና ሥዕላዊ መግለጫዎቻችን /ኢንፎግራፊኮች/ ዘምነዋል። ፈካ ያሉት ቀለሞች እና ግራፊክሱ ውስብስብ መረጃዎችን በቀላሉ ለመረዳት ያስችላሉ። 
ይዘታችን በቀላሉ ወዲያው የሚለይ እና የሚታወቅ እንዲሆን እንዲሁም ድረ ገፃችንን እና መተግበሪያችንን በሚጎበኙበት ጊዜ በአቀራረቡ ይበልጥ እንዲደሰቱ እንፈልጋለን።
 በdw.com ላይ ያለው ለውጥ ገና ጅማሮ ነው። በሚቀጥሉት ወራት የDW ይዘትን ማግኘት በሚቻልባቸው መድረኮች ላይ በሙሉ ተጨማሪ ለውጦች ይደረጋሉ።


የDWን ዲዛይን የበለጠ ማዳበር እንድንችል እባክዎን ተሞክሮዎን ያጋሩን። አስተያየትዎን እንጠብቃለን።


ማኑኤላ ካስፐር ካላሪጅ 
 

 

ማኑኤላ ካስፐር ካላሪጅ 
Manuela Kasper-Claridge As editor-in-chief she's responsible for DW's editorial content across all 32 languages.@ManuelaKC