የ2012 የ ለንደን ኦሎምፒክ
ዓርብ፣ ሐምሌ 20 2004ማስታወቂያ
እ.ጎ.አ የ2012 የለንደን ኦሎምፒክ ዛሬ ከምሽቱ 5 ሰዓት በይፋ ይጀመራል ። ብሪታኒያ ለመክፈቻው ስነስርዓት ብቻ 27 ሚሊዮን ፓውንድ ያወጣችው የብሪታኒያ ባለሥልጣናት የለንደኑ ኦሎምፒክ ወደር አይገኝለትም ሲሉ አስቀድመው ሲያስተዋውቁ ከርመዋል ። በኦሎምፒክ ውድድር መክፈቻ ስነ ስርዓት ላይ 15 ሺህ በጎ ፈቃደኞች ልዩ ልዩ ትርኢቶች በማቅረብ ይሳተፋሉ ። የኦሎምፒክ መክፈቻ ስነ ስርዓት በሚካሄድበት በለንደን መዳረሻው በስታራትፈርድ ስታድየም 62 ሺህ ተመልክቾች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል ። በዓለም ዙሪያም በቢሊዮኖች የሚቀጠር ህዝብ ስነስርዓቱን በቲሌቬዥን ይከታተላል ። ስለ 2012 የለንደን ኦሎምፒክ ዝግጅት የለንደኑን ወኪላችን ድልነሳ ጌታነህን ስቱድዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ አነጋግሬዋለሁ ።
ድልነሳ ጌታነህ
ሂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ