የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ ጉዳይ
ረቡዕ፣ መስከረም 28 2012ማስታወቂያ
ከሰሞኑ አስተዳደሩ በልማት ሰበብ ከመሬታቸው ለተነቀሉ ወገኖች ቤቶቹን በዕጣ ሊሰጥ ነው መባሉን መነሻ በማድረግ ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸው የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር በልማት ምክንያት ይነሱ የነበሩና በአዲስ አበባ ከተማ ዳርቻዎች ይኖሩ የነበሩ አርሶ አደሮች በ20 / 80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች መርሃ ግብር ግንባታ ውስጥ ምትክ ቤት እንዲሰጣቸው የተወሰነው ታህሳስ 24 ቀን 2011 ዓ.ም መሆኑን አመልክተዋል። ይህም በከተማው ካቢኔ ውሳኔ ግንቦት 2011 ዓ.ም ተግባራዊ መደረጉን በመጥቀስ እንደ አዲስ የሚያወዛግብ ነገር አይደለም ሲሉ ዋና ዳይሬክተሩ ኢንጂኒየር ደሳለኝ ተረፈ ተናግረዋል። ሰሎሞን ሙጬ ዝርዝሩን ልኮልናል።
ሰሎሞን ሙጬ
ሸዋዬ ለገሠ
ማንተጋፍቶት ስለሺ