የ2ኛው ዙር የፈረንሳይ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ተፎካካሪዎች
ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 17 2009ማስታወቂያ
ወጣቱ ፖለቲከኛ ኢማኑኤል ማክሮ በአንደኛነት፤ የቀኝ አክራሪው ብሔራዊ ግንባርን ከአባታቸው ተረክበው የሚመሩት ወይዘሮ ማሪን ለ ፔን ሁለተኛ ኾነው ወደ ሁለተኛው ዙር ምርጫ ማለፋቸው ተዘግቧል። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ከሪፐብሊካኖቹ የቀኝ መሀል ወይንም ከሶሻሊስቶቹ ግራ መሀል ፓርቲዎች አንዱ እንኳን ለሁለተኛው ዙር ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ማለፍ አለመቻሉ ብዙዎችን አስደምሟል። የዛሬው አውሮጳ እና ጀርመን የሚያጠነጥነው በምርጫዉ ዉጤትና በሁለቱ መሪዎች ላይ ነው።
ገበያው ንጉሤ
ነጋሽ መሀመድ