የ G7 ጉባኤ ጀመረ
እሑድ፣ ግንቦት 30 2007ማስታወቂያ
የጀርመን የዩኤስ አሜሪካ፤ የካናዳ፤ የፈረንሳይ፣ የጃፓን፣ የኢጣልያ እና የብሪታንያ ፖሊተከኞች የሚካፈሉበት ይህ የሁለት ቀን ጉባኤ በተለይ በከባቢ አየር ጉዳይ ለማስጠበቅ ፤ አሸባሪነትን ለመዋጋት እንዲሁም በዓለም የንግድ ጉዳይ ላይ እንደሚመክሩ ይጠበቃል። ጉባኤዉ ከመጀመሩ በፊት የጀርመንዋ መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል የዩኤስ አሜሪካዉን ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማን ተቀብለዉ አነጋግረዋል። ሁለቱም መሪዎች የሁለቱን ሃገራት ግንኙነት አስፈላጊነት አስመርዉበታል። በሌላ በኩል ይህንን ጉባኤ በመቃወም ጉባኤዉ በሚካሄድበት አቅራቢያ በሚገኝ አነስተኛ ከተማ ከፍተኛ የተቃዉሞ ሰልፍ ተካሂዶአል። እንደ ብዙኃም መገናኛዎች ዘገባ ይህን ጉባኤ ደህንነት ለማስጠበቅ ወደ 20 ሺ ፀጥታ አስከባሪዎች ተሰማርተዋል፤ ወደ 3000 ሺህ የሚሆኑ ጋዜጠኞች ደግሞ ለዘገባ ቦታዉ ላይ ይገኛሉ።
አዜብ ታደሰ
ልደት አበበ