የ ተ መ ድ 5ኛው የአየር ንብረት ለውጥ ዘገባ
ረቡዕ፣ መስከረም 29 2006ሊያጋጥም ይችላል ሲል በማስታወሻው ላይ ማሥፈሩየሚጠቀስ ነው። መንግሥታት ተገቢውን የማስተካከያ እርምጃ ካልወሰዱ ፣ ትንበያው በአርግጥ የማይፈጸምበት ምክንያት አይኖርም። ያለፈው ሰሞን ማስጠንቀቂያም፣ ጎርጎሪዮሳዊው 2100 ከመድረሱ በፊት ለጥፋት የሚዳርግ አደጋ ተጋርጧል ነው ያለው።
በአሁኑ ዘመን ፣ የዓለም ሕዝብ ቁጥር 7 ቢሊዮን መድረሱ ከታወቀ ወዲህም ቢሆን፣ በፍጥነት እየጨመረ በመኼድ ላይ መሆኑ እሙን ነው። የህዝብ ቁጥር መጨመር ደግሞ በፕላኔታችን ላይ ከባድ ጫና ማሳረፉ የሚያጠራጥር አለመሆኑን ብቻ ሳይሆን፣ የሰዎች ጥንቃቄ የጎደለው እርምጃ፣ምድራችንን ለጥፋት የሚዳርግ ብርቱ የአየር ንብረት ለውጥ እንደሚያስከትል፣ ከመስከረም 13-16, 2006 ፤ በአስቶክሆልም እስዊድን የተካሄደው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በይነ መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ነክ ም/ቤት፤ በአንግሊዝኛው አሕጽሮት (IPCC) ማስገንዘቡ የሚታወስ ነው። የምድራችን ግለት እጨመረ መኼድ፤ በሰሜንና በደቡብ የምድር ዋልታ አካባቢ በተለያዩ ደሴቶችና በባህር ጠረፎች፤ ሊያጋጥም ስለሚችለው አደጋ በአየር ንብረት ላይ ያተኮሩ የሳይንስ ጠበብት 5ኛውን ዘገባይፋ ባደረጉበት ሰነድ ላይ ሳያስገነዝቡ አላለፉም።
በሌሎች የዓለም ክፍሎች፤ እዚህም ላይ በሰሜን ምሥራቃዊው አፍሪቃ ወይም በኢትዮጵያ ፣ በዚህ ረገድ ምንድን ነው የሚያሠጋው አደጋ? አደጋውንስ ለመቋቋም ምንድን ነው መደረግ ያለበት? የ 110 ሃገራት ተወካዮች በተገኙበት የአስቶክሆልሙ ጉባዔ ኢትዮጵያን ወክለው በዚያ የተሳተፉትን የአየር ንብረት ጉዳይ ባለሙያ አነጋግረናል ።
በቅርቡ በአስቶክሆልም በተካሄደው ጉባዔ፣ የአየር ንብረት ተመራማሪዎች ፣ ለዓለም መንግሥታት ያቀረቡት የጥናት ውጤት ዋና መልእክትም ሆነ ማስጠንቀቂያ ምንድን ነው?
በኢትዮጵያ ብሔራዊ የአየር ጠባይ ጥናት ድርጅት(ኤጀንሲ) የአየር ጠባይ(ሚቲዮሮሎጂ) ትንበያና ማስጠንቀቂያ የሥራ አመራር ዋና ኀላፊ(ዳይሬክተሬት ዳይሬክተር) አቶ ድሪባ ቆሪቻ--
ተክሌ የኋላ
ሸዋዬ ለገሰ