የፖለቲካ ምሁርና የSPD ፖለቲከኛ ባለቤት
ሐሙስ፣ ጳጉሜን 5 2001ማስታወቂያ
በዚህ ፌደራዊ ክፍለ ሀገር በቅርቡ በተካሄደ ምርጫ ውጤት ሶስተኛ ደረጃ ያገኙት የSPD ው ክሪስቶፍ ማቺም በዚህ ግዛት በሚመሰረተው ተጣማሪ መንግስት ውስጥ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆን ከሚችሉት የፓርቲ መሪዎች አንዱ ናቸው ።የኚህ ታዋቂ የጀርመን ፖለቲከኛ ባለቤት ፣ ዶክተር ምፅላል ክፍለ እየሱስ በዛሬው አውሮፓ እና ጀርመን ዝግጅታችን የስራና የህይወት ልምዳቸውን ያካፍሉናል ። ሰፊውን ጊዜ ወደ ሚይዘው ወደ ዚህ ቃለ ምልልስ ከማለፋችን በፊት ስፓኝ ስራ አጥ የውጭ ዜጎች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ስለጀመረችው መርሀ ግብር ጥቂት እናወሳለን ።
ሂሩት መለሰ