የፌደሬሽን ምክር ቤት ዉሳኔና ተቃዋሚዎች
ረቡዕ፣ ሰኔ 3 2012ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ ዉስጥ በመጪዉ ነሐሴ ሊደረግ ታቅዶ የነበረዉ ምርጫ መራዘሙን የሐገሪቱ የፌደሬሽን ምክር ቤት ዛሬ አፀደቀዉ።ለነሐሴ ተይዞ የነበረዉ ምርጫ የተሰረዘዉ በኮሮና ተሕዋሲ ስርጭት መሐል ምርጫ ማድረግ አይቻልም በሚል ነዉ።ምክር ቤቱ በዛሬዉ ጉባኤዉ የኮሮና ተሕዋሲ ስርጭት መቀነሱ ከተረጋገጠ፣ ምርጫዉ ከ9 ወራት እስከ 1 ዓመት ባለዉ ጊዜ እንዲደረግ ወስኗል።ምርጫ እስኪደረግ በስልጣን ላይ ያለዉ መንግሥት ከነሙሉ መዋቅሮቹ የያዘዉን ስልጣን እንደያዘ ይቀጥላል።የምክር ቤቱን ዉሳኔ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ከጥርጣሬና ትችት ጋር ተቀብለዉታል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ነጋሽ መሐመድ
አዜብ ታደሰ