የፋታህ ማዕከላዊ ኮሚቴ ምርጫ
ረቡዕ፣ ነሐሴ 6 2001ማስታወቂያ
ፓርቲው ባለፈው ሳምንት በቤተልሄም ከተማ ካለፉት ሀያ ዓመታት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ባካሄደው ጉባዔው ላይ ሀያ አንድ አባላት ከሚያጠቃልለው የማዕከላዊ ኮሚቴ መካከል ሁለት ሶስተኛውን በትናንቱ ዕለት የመረጠ ሲሆን መርጦዋል። ክሌመንስ ፈሬንኮተ እንደዘገበው፡ ብዙ ወጣት ተመራጮችን ባስገኘው ምርጫ ከተመረጡት መካከል በእስራኤል ወህኒ ቤት የሚገኙትና ፕሬዚደንት ማህሙድ አባስን የመተካት ዕድል አላቸው የሚባሉት የሀምሳ ዓመቱ ማርዋን ባርጉቲ ይገኙበታል።
ክሌመንስ ፈሬንኮተ/ይልማ ሀይለሚካኤል/ሸዋዬ ለገሠ