የጥቁር ሰው አልበም ምረቃ
ረቡዕ፣ ግንቦት 29 2004ማስታወቂያ
ተወዳጁ አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን ወይም ቴዲ አፍሮ ፣«ጥቁር ሰው» በሚል ርዕስ በቅርቡ ያወጣውን ዘፈንና የዘፈኑን ማጀቢያ ፊልም ትናንት ምሽት በሂልተን ሆቴል አስመርቋል ።
«ጥቁር ሰው »ቴዲ አፍሮ ለመላዉ ጥቁር ህዝብ ኩራት ያቀዳጀዉን የአድዋ ድል በማዘከር፤ ዳግማዊ ሚኒልክንና በአድዋ ጦርነት የተጋደሉትን የጦር መሪዎቻቸውን ያወደሰበት የሙዚቃ ሥራ ነው። ለሥራው ወደ ግማሽ ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብ እንደወጣ እና ከ450 በላይ ተዋንያንም እንደተሳተፉበት ወኪላችን ታደሰ እንግዳው ዘግቧል ።
ታደሰ እንግዳው
ሂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሰ