የጥላቻ ንግግርና ማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ላይ የመከረው መድረክ
ቅዳሜ፣ የካቲት 16 2011ማስታወቂያ
በብሄር አደረጃጀት የተዋቀረው የሃገሪቱ የፖለቲካ ስርአተ ማህበር የችግሩ ዋነኛ ምንጭ በመሆኑ የህግ ማእቀፎችን ከማውጣት በላይ መዋቅሩ ላይ መስራት እንደሚገባም የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ፕሮጀክት ከካናዳ ኤምባሲ ጋር በመተባበር ስለ ጥላቻ ንግግር ምንነ፤ የጥላቻ ንግግር በኢትዮጵያ ሕግ ማእቀፍ እንዴት ይታያል፤ የማኅራዊ ሚዲያ መስፋት አጠቃቀም እና የጥላቻ ንግግር አዝማሚያዎች ምን ይመስላሉ? በሚሉ እና ከማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምጋር በተገናኙ ያሉ ክፍተቶችን ለመዳሰስ ዛሬ ውይይት ተደርጓል። ብሄርን እንደ አቀጣጣይ ነገር መጠቀም፤ ከዚህ በፊት ተበድያለሁ የሚል ስሜት ማደግ እና የማኅበራዊ መገናኛዎችን በስፋት የመጠቀም ባህል እያደገ መምጣት ችግሩን ተቆጣጣሪ አልባ እያደረገው መሆኑም በውይይቱ ተዳስሷል፡፡ የብሄር ማንነትን እንደ ስነልቦናና ማህበራዊ ወሳኝ እሴት በማየት ቋንቋ የሚጎለብበት፤ ባህል የሚዳብርበትና ታሪክ ጥበቃ የሚደረግበት ተቋማዊ ቅርጽ መፍጠር ለችግሩ መቃለል እንደመፍትሄ ተቀምቷል በውይይቱ፡፡
ሰለሞን ሙጪ
እሸቴ በቀለ