የጣልያን የፖለቲካ ቀዉስ
ዓርብ፣ ነሐሴ 17 2011ማስታወቂያ
ጠቅላይ ሚኒስትር ኮንቴ የኢጣሊያን የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ማቲዮ ሳልቪኒ የገዢውን ጥምረት አፍረክረከዋል፤ የሀገሪቱንም ኢኮኖሚ ለአደጋ አጋልጠዋል ሲሉ ወርፈዋቸዋል። ኮንቴ ባለፈዉ ማክሰኞ ሥልጣናቸውን እንደሚለቁ ለምክር ቤቱ ሲናገሩ፣ በተጣማሪነት የሚሠሩት የቀኝ ክንፍ ሊግ እና የአምስት ኮከብ እንቅስቃሴ የተባለው ፓርቲን ትስስር የሚያናጋ ርምጃ ወስደዋል በሚል ሳልቪኒን ከሰዋል። ኢጣልያ ዉስጥ መንግሥት ባጭር ጊዜ ዉስጥ ስልጣን መልቀቅ እንደ ልማድ የሚታይ ነዉ።የሮሙ ዘጋብያችን ተኽለግዚ ገብረየሱስ እንደሚለዉ የጣልያኑ ፕሬዚዳንት ሰርጂዮ ማታሬላ በመጪዉ ሳምንት ሁለቱን ትልልቅ ፓርቲዎች መሪዎች ጠርተዉ ያነጋግራሉ፤ ፓርቲዎቹ ጥምር መንግሥት ለመመስረት ካልወሰኑ ግን፤ ብሔራዊ ምርጫ ይካሄዳል።
ተኽለዝጊ ገብረየሱስ
አዜብ ታደሰ