1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጣልያን አፍሪቃ የመሪዎች ጉባኤ በሮም

ረቡዕ፣ ጥር 22 2016

ጉባኤውን ተንተርሰው የጣልያን ጋዜጦች በርካታ ጉዳዮች የዘገቡ ቢሆንም በተለይ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትርና የሶማልያው ፕረዚደንት ለማነጋደር ሙከራዎች እንደነበረ፤ የሶማልያው ፕረዚደንት ለአንድ የጣልያን ጋዜጣ በሰጡት መግለጫም ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር ያደረገችው የወደብ ኪራይ የመግባቢያ ሰነድ ፊርማ ቀጠናውን የሚያተራምስ በማለት አጣጥለውታል።

https://p.dw.com/p/4bt6X
Italien-Afrika Gipfel in Rom
ምስል Remo Casilli/REUTERS

የአፍሪቃ ጣልያን የመሪዎች ጉባኢ

የአፍሪቃና ጣልያን የመሪዎች ጉባኤ ላይ የ22 ሃገራት መሪዎችና ተወካዮች በተገኙበት ሰሞኑ በሮም ከተማ ተካሂዷል። የጉባኤው ዓላማ ጣልያን ብሎም አዎጳ ከአፍሪቃ ጋር በጋራ ለማደግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ለመምከር ነው ተብሏል። የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ እንዳሉት ሃገራቸው ከአፍሪቃ ሃገራት ጋር በተለይም በጤና፣ በትምህርትና በሃይል በኩል በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳላት ገልጸዋል።

የጣሊያን-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ : የሜሎኒ እቅድ እና ፈተናዎቹ ጉባኤውን ተንተርሰው የጣልያን ጋዜጦች በርካታ ጉዳዮች የዘገቡ ቢሆንም በተለይ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትርና የሶማልያው ፕረዚደንት ለማነጋደር ሙከራዎች እንደነበረ፤ የሶማልያው ፕረዚደንት ለአንድ የጣልያን ጋዜጣ በሰጡት መግለጫም ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር ያደረገችው የወደብ ኪራይ የመግባቢያ ሰነድ ፊርማ ቀጠናውን የሚያተራምስ በማለት አጣጥለውታል። 


የድምጽ ማዕቀፉን በመጫን ከሮም ወኪላችን ተኽለእግዚ ገብረእየሱስ ጋር ያደረግነውን አጭር ቆይታ ማዳመጥ ትችላላችሁ።


ተኽለእግዚ ገብረእየሱስ
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር
አዜብ ታደሰ