1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ፣ ኢትዮጵያ ወደብ ያስፈልጋታል አቋም በተንታኞች ዕይታ

ረቡዕ፣ ኅዳር 5 2016

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ የአፍሪቃ ቀንድ ሁኔታ የፈጠረው ሥጋት፣ ኃያላን ሀገራት ጅቡቲ ላይ ትልልቅ ወታደራዊ ካምፖች ያሏቸው በመሆኑ ሀገራቱ ግጭት ውስጥ ቢገቡ ኢትዮጵያ የምትገባበትን ፈተና በመጥቀስ "ብቸኛ መተንፈሻችን ነው" ያሉትን ቀይ ባህርን እና የጎረቤት ሀገራትን ወደቦች በንግድ ሕግ መሠረት የመጠቀም ፍላጎት እንዳለ ደጋግመው ሲያነሱ ቆይተዋል

https://p.dw.com/p/4YqLN
Äthiopien Abiy Ahmed
ምስል Amanuel Sileshi/AFP

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፣ ኢትዮጵያ ወደብ ያስፈልጋታል አቋም በተንታኞች እይታ

በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ ላይ የተንታኞች አስተያየት

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ "የአካባቢው የፖለቲካ ሁኔታ መበላሸት" ሲሉ የገለፁት የአፍሪካ ቀንድ ሁኔታ የፈጠረው ሥጋት፣ ኃያላን ሀገራት ጅቡቲ ላይ ትልልቅ ወታደራዊ ካምፖች ያሏቸው በመሆኑ ሀገራቱ ግጭት ውስጥ ቢገቡ ኢትዮጵያ የምትገባበትን ፈተና በመጥቀስ "ብቸኛ  መተንፈሻችን ነው" ያሉት ቀይ ባህርን እና የጎረቤት ሀገራትን ወደቦች በንግድ ሕግ መሠረት የመጠቀም ፍላጎትን ደጋግመው አንስተዋል።"ኢትዮጵያ ወደ ኤርትራ ፣ ወደ ሶማሌ ፣ ወደ ጅቡቲ፣ ወደ ኬንያ ወይም ወደ ሌላ ጌረቤቶቻችን አንድም ጥይት የመተኮስ ፍላጎት የላትም፣ በሉአላዊነታቸው ላይም ጥያቄ የላትም። እያልን ያለነው በአፍሪካ ምርጥ አየር መንግድ አለን እሱን እንጋራ እና ውኃ አጋሩን፣ በአፍሪካ አንደኛውን ግድብ ገንብተናል፣ እሱን እንጋራና አጋሩን ነው"  በጉዳዩ ላይ ሀሳባቸውን የጠየቅናቸው የምጣኔ ሀብት ባለሙያው አቶ ክቡር ገና ነገሩ "የቤተሰብ ጉዳይ" እንዳልሆነና አሰራሩም የተልመደ አለመሆኑን ጠቅሰዋል።«ከመገዳደል መገዳደር» ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ"ወደብ ማስፈለጉ ግልጽ ቢሆንም ያለወደብ እስከዛሬ ድረስ ኖረንም እድገት ያሳየንበት ወቅት አለ። የቤተሰብ ጉዳይ አይደልም ፣ የተለመደ እሰራርም ስላልሆነ በተለይ በአሁኑ ጊዜ ትክክል ነው ብየ አላስብም" ብለዋል።  

Äthiopien Parlament Addis Abeba
ኤርትራ ነፃነቷን አውጃ ከኢትዮጵያ ከተለየች ወዲህ ወደብ አልባ ከሆኑ 16 የአፍሪካ ሀገራት አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ የወጪ ንግድ እንቅስቃሴዋ በጅቡቲ ላይ የተንጠለጠለ ሆኗል ምስል Solomon Muche/DW

ወደብ ለማግኘት የሀገራት መተማመን ወሳኝ ነው

ሌላኛው የጠየቅናቸው የአለም አቀፍ ሕግ እና ዲፕሎማሲ ተንታኝ አለም አቀፍ የውኃ አጠቃቀም ሕግ "የትኛውም ሀገር ወደብ አልባ የሆኑ ሀገራትን ወደብ እንዳይጠቀሙ መከልከል አይችልም" ሲሉ የሕጉን ጭብጥ አብራርተዋል።ለፓርላማው የዓለም መንግስታት ሊያግዙ እንጂ ሊያራግቡ አይገባም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በጉዳዩ ላይ መወያየት የሚፈል ጎረቤት ሀገር ካለ መንግሥት በማንኛውም ጊዜና ቦታ ለመነጋገር ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል።

 "የትኛውም ሀገር ወደብ አልባ የሆኑ ሀገራትን ወደብ እንዳይጠቀሙ መከልከል አይችልም" ሲሉ የሕጉን ጭብጥ አብራርተዋል።ለፓርላማው የዓለም መንግስታት ሊያግዙ እንጂ ሊያራግቡ አይገባም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በጉዳዩ ላይ መወያየት የሚፈል ጎረቤት ሀገር ካለ መንግሥት በማንኛውም ጊዜና ቦታ ለመነጋገር ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ "የአካባቢው የፖለቲካ ሁኔታ መበላሸት" ሲሉ የገለፁት የአፍሪካ ቀንድ ሁኔታ የፈጠረው ሥጋት፣ መንስኤ "ብቸኛ  መተንፈሻችን ነው" ያሉት ቀይ ባህርን እና የጎረቤት ሀገራትን ወደቦች በንግድ ሕግ መሠረት የመጠቀም ፍላጎትን ደጋግመው አንስተዋል።ምስል Facebook.com/Office PM Ethiopia

በጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ የወደብ ሃሳብ ሰዎች ምን አሉ?አቶ ክቡር ገና እንደሚሉት ግን ጉዳዩ ቀድሞውኑ ንግግር የሚሻ ነው። የጉዳዩ ባለቤት ሀገራት መተማመን የግድ ያስፈልጋቸዋል የሚለው ደግሞ የአለምአቀፍ ሕግ ተንታኙ ሀሳብ ነው።ባለሙያው እንደሚሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቀረቡት ጥያቄ ተገቢነት ያለው የመሆኑን ያህል መቅደም ያለበት ሥራ አልተሠራም።"ስለዚህ አጀንዳ ማውራት እንድ ነገር ነው። ምቹ ከባቢ ፈጥሮ ነው ሊገለጽ ይሚገባው። ከዚያ ውጪ በሕዝብ አደባባይ ይሚባሉ ነገሮችም የሚፈጥሩት ጉዳት አለ። ምክንያቱም ይህ በዲፕሎማሲ ግንኙነት የሚገኝ ጥቅም ነው" ኤርትራ ነፃነቷን አውጃ ከኢትዮጵያ ከተለየች ወዲህ ወደብ አልባ ከሆኑ 16 የአፍሪካ ሀገራት አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ የወጪ ንግድ እንቅስቃሴዋ በጅቡቲ ላይ የተንጠለጠለ ሆኗል 

ሰሎሞን ሙጬ 

ኂሩት መለሰ

ታምራት ዲንሳ