የጠ/ሚሩ ዉሳኔና የተቃዋሚ ፓርቲዎች አስተያየት
ሐሙስ፣ የካቲት 8 2010ማስታወቂያ
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ዛሬ ቀትር ላይ በቴሌቭዝን መስኮት ቀርበዉ የስልጣን መልቀያ ማቅረባቸዉ እንብዛም ያልተጠበቀ እንዳልሆነ የፖለቲካ ተቃዋሚዎች ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ሕዝብ መንግሥት ስልጣን ይልቀቅ ነዉ የሚለዉ ሲሉ አስተያየታቸዉ የሰጡን የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) ባጭሩ ምክትል ሰብሳቢ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ፤
በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን የመከላከያ ሠራዊትን በተመለከተ ልዩ ፕሮግራሞች እየቀረቡ ስለነበረ አንዳንድ ነገር እንደሚከሰት ይሸት ነበር ሲሉ የገለፁት የቀድሞ የፓርላማ አባል አቶ ልደቱ አያሌዉ ናቸው።
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ በበኩላቸዉ ሥራቸዉን በተለያየ ምክንያት መፈፀም ባለመቻላቸዉ መልቀቃቸዉ አስደናቂ አይደለም ነው ያሉት።
አዜብ ታደሰ
ሸዋዬ ለገሠ