የግሪክ ፖለቲካዊ ቀዉስና አዉሮጳ
ሐሙስ፣ ግንቦት 2 2004ማስታወቂያ
ባለፈዉ ዕሁድ ግሪክ ዉስጥ በተደረገዉ ምርጫ ከፍተኛዉን ድምፅ ያገኙት ሁለት የፖለቲካ ፓርቲዎች መንግሥት ለመመሥረት ያደረጉት ጥረት ከሸፈ።የመጀመሪያዉን ደረጃ የያዘዉ አዲሱ ዲሞክራሲ የተሰኘዉ የመሐል-ቀኝ ፓርቲና ሁለተኛዉ፥ ሲረዛ የተሰኘዉ የግራ ፅንፈኛዉ ፓርቲ መንግሥት ለመመሥረት በየተራ ያደረጉት ሙከራ ያለዉጤት በማብቃቱ፥ የሰወስተኝነቱን ደረጃ የያዘዉ የሶሻሊስቱ ፓርቲ ዛሬ ሌላ ሙከራ ጀምሯል።ሙከራዉ ካልተሳካ ካንድ ወር በሕዋላ ሌላ ምርጫ ይደረጋል።የግሪክና የፈረንሳይ ምርጫ በአዉሮጳ የቁጠባ መርሕ ላይ ያስከተለዉ ተፅዕኖ ግን አሁንም እያነጋገረ ነዉ።ገበያዉ ንጉሴ ከብራስልስ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።
ገበያዉ ንጉሴ
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሠ