የግሪክ አበዳሪዎች የደረሱበት ስምምነት
ሰኞ፣ ሐምሌ 6 2007ማስታወቂያ
የትናንት ሌሊቱ ጉባኤ ለግሪክ የብድር ጥያቄ የመጨረሻ ውሳኔ ከመስጠት ባሻገር፤ ግሪክ በዩሮ ዞን ትቆይ ወይስ ለተወሰኑ ዓመታት ለቃ ትውጣ የሚሉ ጥያቄዎችም ያስተናገደ ነበር። ግሪክ ከአበዳሪዎቿ የተጣሉባትን ቅድመ ሁኔታዎች በመቃወሟ የብድር እና ርዳታ መርሃ ግብሮች ተቋርጠው ፤ የግሪክ ባንኮች ተዘግተው መሰንበታቸው ይታወሳል። ግሪክ በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት ከ82 እስከ 86 ቢሊዮን ዮሮ ብድር እንድታገኝ አበዳሪዎቿ ቢፈቅዱም፤ የግሪክ ፓርላማ አበዳሪዎቿ አያይዘው ያቀረቡትን ቅድመ ሁኔታ እስከ እሮብ ድረስ ማፅደቅ ይኖርበታል። የግሪክ ተጨማሪ የብድር ጥያቄን አስመልክቶ ባለፉት ሁለት ቀናት ብራስልስ የተካሄደውን የዩሮ ሸርፍ አባል ሃገራት የገንዘብ ሚኒስትሮች እና የአውሮፓ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ፤ በስፍራው የሚገኘው ገበያው ንጉሴ ተከታትሏል።
ገበያው ንጉሴ
ልደት አበበ
አርያም ተክሌ