የጋዜጠኛ ተመሥገን ደሳለኝ እናት አቤቱታ5 የካቲት 2007ሐሙስ፣ የካቲት 5 2007ካለፈው ጥቅምት ወር ወዲህ በእስራት የሚገኘው ጋዜጠኛ ተመሥገን ደሳለኝ እናት ወይዘሮ ፋናዬ እርዳቸው ልጃቸውን መጠየቅ እንዲችሉ በመጠየቅ ለጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤት እና ለፌዴራል የሕዝብ እንባ ጠባቂ ኮሚሽን፣ እንዲሁም ለውጭ ሀገር ኤምባሲዎች ደብዳቤ መላካቸውን አስታወቁ።https://p.dw.com/p/1EaBiምስል DWማስታወቂያ ጋዜጠኛው ካለፈው አንድ ወር ጀምሮ በቤተሰብ እንዳይጎበኝ መደረጉን ወይዘሮ ፋናዬ ለዶይቸ ቬለ ገልጸዋል። የፌዴራል የሕዝብ እንባ ጠባቂ ኮሚሽን የተባለው ደብዳቤ እንደደረሰው እና ጉዳዩን በማጣራት ላይ እንደሆነ አመልክቶዋል። ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር አርያም ተክሌ ተክሌ የኋላ