1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጋና ምርጫ እና የዕጩ ፕሬዚደንቶች የምርጫ ዘመቻ አንድምታ

ቅዳሜ፣ ጥቅምት 16 2017

ጋና የፊታችን የታህሳስ ወር ለምታደርገው ምርጫ ብርቱ ተፎካካሪ ሆነው የቀረቡት የገዢው ፓርቲ ዕጩ መሐመዱ ማዉሚያ እና የተቃዋሚ ፓርቲ ዕጩው ጆን ድራማኒ የጦፈ የምረጡኝ ዘመቻቸውን ተያይዘውታል ።

https://p.dw.com/p/4mGN1
Kombobild | Mahamudu Bawumia und John Dramani Mahama
ምስል NIPAH DENNIS/AFP/Getty Images | OLYMPIA DE MAISMONT/AFP

ተጠባቂው የጋና ምርጫ እና የዕጩዎች ቅስቀሳ

ጋና የፊታችን የታህሳስ ወር ለምታደርገው ምርጫ ብርቱ ተፎካካሪ ሆነው የቀረቡት የገዢው ፓርቲ ዕጩ መሐመዱ ማዉሚያ እና የተቃዋሚ ፓርቲ ዕጩው ጆን ድራማኒ  የጦፈ የምረጡኝ ዘመቻቸውን ተያይዘውታል ።

የወቅቱ የጋና ምክትል ፕሬዚዳንት እና የገዢው ፓርቲ New Patriotic Party (NPP) ዕጩው መሐመዱ ማዉማ የፕሬዚደንትነት መንበሩን ለመቆናጠጥ እንዲሁም የተቃዋሚ ፓርቲው National Democratic Congress (NDC) ዕጩው ጆን ድራማኒ ማህማ በድጋሚ ወደ ስልጣን የሚመለሱበትን ዕድል ለማመቻቸት በየፊናቸው ቃል እየገቡ ነው።

የምርጫ ዘመቻው ወደ ፊት ገፍተው ለመጡት ሁለቱም ዕጩዎች ቀላል እንደማይሆን ሲጠበቅ የጋናዉያንንን ልብ እናሸፍትበታለን አልያም ልዩነት እንፈጥርበታለን ያሉትን አማራጭ ፖሊሲዎችን እያስተዋወቁ  ቅስቀሳቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል።

የተቃዋሚ ፓርቲ መሪው ጆን ድራማኒ ከጎርጎርሳዉያኑ 2013 -17 ለአራት ዓመታት ጋናን ካስተዳደሩ ወዲህ በድጋሚ ለመመረጥ ሶስት ያህል ጊዜ ብርቱ ትግል ቢያደርጉም አልተሳካላቸውም።

ተሰናባቹ ፕሬዚዳንት ናና አኩፎ አዶ ሁለት የስልጣን ዘመናቸውን በማጠናቀቃቸው ምክትላቸውን የፓርቲው ዕጩ አድርገው ይሰናበታሉ ።

ዘንድሮ የሚካሄደው የጋና ምርጫ

አሁን ውድድሩ በወቅቱ ምክትል ፕሬዚዳንት እና በተከታታይ የምርጫ ዓመታት ስኬት ከራቃቸው የተቃዋሚ ፓርቲ መሪው ጋር ይሆናል ማለት ነው።

ለመሆኑ ዕጩ ፕሬዚዳንቶቹ በየፊናቸው የጋናዉያንን ልብ ለማሸፈት ይዘው እየተንቀሳቀሱ የሚገኙት የዘማቻ ስልታቸው የት ያደርሳቸው ይሆን ? ለጋናዉያንስ ምን የተለየ ነገር ይዘው ይመጡ ይሆን ?

የጋናን ፖለቲካ በቅርበት የሚከታተሉት እና የሚተነትኑት ኢብራሂም አልሃሰን እንደሚሉት ሁለቱ የጋና ዋነኛ ተቀናቃኝ ፓርቲዎች በየምርጫ ዘመቻዎቻቸው በብዙ ተግዳሮቶች ውስጥ  አሳልፏቸዋል። ለዚህ ነው ሁለቱም የተቀናጀ የምርጫ ዘመቻ ስልትን ለመከተል የወሰኑት ይላሉ ።

በጋና የምርጫ ዘመቻ
የጋናን ፖለቲካ በቅርበት የሚከታተሉት እና የሚተነትኑት ኢብራሂም አልሃሰን እንደሚሉት ሁለቱ የጋና ዋነኛ ተቀናቃኝ ፓርቲዎች በየምርጫ ዘመቻዎቻቸው በብዙ ተግዳሮቶች ውስጥ  አሳልፏቸዋል። ለዚህ ነው ሁለቱም የተቀናጀ የምርጫ ዘመቻ ስልትን ለመከተል የወሰኑት ይላሉምስል NIPAH DENNIS/AFP

“እኔ እንደማስበው ባለፉት ዓመታት በተደረጉት ዘመቻዎች፣ በተለይ ሁለቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ አንዳንድ ለውጦችን ያሳለፉ ናቸው። ስለዚህ ከሁለቱም ኤን ዲ ሲ እና ኤን ፒ ፒ ፓርቲዎች በተነገረን በተቀናጀ የዘመቻ ስልት ወይም በተናጥል ዘመቻ የማካሄድ ስልት እንዲከተሉ ወስነዋልይህ ደግሞ ትልልቅ ስብሰባዎችን መጥራት አይጠበቅባቸውም ማለት ነው ።  »

እንደ አልሃሰን አሰተያየት ዕጩዎች ከተለመደው በርካታ ሰዎችን የሚያሳትፉ ሰልፎችን ከመጥራት ይልቅ ማህበረሰብን መሰረት ያደረገ አካሄድን መምረጣቸውን ነው ያመላከተው። ይህ ደ,ግሞ ሁለቱም አንድ አይነት የምርጫ ስልት መከተላቸውን እና ውድድሩን የበለጠ ተጠባቂ ሊያደርገው እንደሚችል ነው ተንታኙ የተመለከቱት።

በናይጀሪያ የተስፋፉት የሀሰት የዩኒቨርስቲ ዲግሪዎች

«ሁለቱም ዋነና ፓርቲዎች ይህንኑ ሲገፉበት ነው የቆዩት ። ለምሳሌ ኤን ዲ ሲን ያየህ እንደሆነ የ24 ሰዓት ኤኮኖሚ ያለውን የማሻሻያ መርህ ይዞ  በዚሁ ነው እየገፋ ያለው ። የኤን ፒ ፒው ዲጅታላይዜሽንም የተከተለው መንገድም በሁለቱ መካከል መገፋፋት መኖሩን ነው የሚያሳየው። በጥቅሉ ግን የምርጫ ቅስቀሳው ቃል ሁለቱም ፓ ፓርቲዎች ከሞላ ጎደል አንድ አይነት መሆናቸውን የታዘብኩት ነገር ነው።» 

ሲሉ ተናግረዋል።

 ከዓለም አቀፍ አበዳሪዎች 30 ቢሊዮን ዶላር ዕዳ ያለባት ጋና ይህንኑ የውጭ ዕዳዋን መክፈል ተስኗት መቆየቷ ነው የሚነገረው ። በ,ዚህ እና በሌሎች ምክንያቶች የተዳከመውን ኤኮኖሚዋን ወደ ነበረበት ለመመለስም በዓለም የገንዘብ ድርጅት አይ ኤም ኤፍ መርኃ ግብር ስር ለመታቀፍ ተገዳለች። ዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት ለጋና የ3 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ሀገሪቱ ከዕዳዋ እንድታገግም እና በመልሶ ማደራጀት መክፈል እንድትችል ያግዛታል ነው ፤ የተባለው።

የኤን ዲ ሲ ዕጩው በምርጫ ዘመቻቸው ይዘውት ከቀረቡት አንዱ በሆነው በዲጂታል ፈጠራ የ24 ሰዓት ኤኮኖሚ የተሰኘው ጽንሰ ሃሳብ አንዱ እና ምናልባትም ጋና ለገባችበት የኤኮኖሚ ውድቀት ትንሳኤ ይዞላት እንደሚመጣ ተስፋ የሚያደርጉ ጥቂቶች አይደሉም።

የኤኮኖሚ ባለሞያ እና  የቀድሞ የማዕከላዊ ባንክ ሰራተኛ የነበሩት እና የተቃዋሚ ፓርቲ ዕጩ ፕሬዚዳንት ባውሚያ ስለ ዲጂታል ፈጠራ ፖሊሲዎች ለጋና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ቁልፍ መፍትሄዎች እንደሆኑ ተናግረዋል ።

የዴሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ኮንጎ ግጭት መባባስ ያስከተለው ስጋት

ባውሚያ በጋና ደቡብ ምስራቅ ቮልታ ክልል በተካሄደው የምርጫ ዘመቻ  ላይ "ሁሉም ወጣቶች፣ ስራ ይፈልጋሉ። ለዚህ ደግሞ በጋና ውስጥ ለአንድ ሚሊዮን ወጣቶች ዲጂታል ክህሎት እሰጣለሁ" ሲሉ ተደምጠዋል። ዕጩው አጓጊ በሚመስለው ቅስቀሳቸው ዕድሉን ለማንኛውም ሰው ትምህርት የቋረጡ ወጣቶችም ቢሆኑ የዲጂታል ክህሎት ስለጠናው ተቋዳሽ እንዲሆኑ የሚጋብዝ ነው ። ።

የገዢው ፓርቲ ዕጩ ማሃማ በበኩላቸው የጋናን የኤኮኖሚ በር ይበረግዳል ያሉትን የምርጫ ቅስቀሳ ሃሳባቸውን ሲያቀርቡ ጋናዉያን ከመደበኛ የስራ ሰዓታቸው ውጭ ጭምር በ,ኤኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ተሳታፊ እንዲሆኑ ይጋብዛሉ። ይህ ደግሞ ሰራተኞች በተለያዩ የስራ መስኮች እንዲሳተፉ ድርጅቶችም ተጨማሪ የሰው ኃይል እንዲቀጥሩ ዕድል ይፈጥርላቸዋል።

እንደዚያም ሆኖ ግን ከቀረበለት የሃሳብ ምርጫ በድምጹ ሊወስን ያለው እያንዳንዳንዱ ጋናዊ የትኛውን እንደሚመርጥ ውሳኔው የራሱ ይሆናል። ተፎካካሪዎች አጠናክረው ከቀጠሉት ከምረጡኝ ዘመቻቸው ከወዲሁ ተረድተው ሃሳባቸውን ያካፈሉም አልጠፉም ።

ምርጫ ጋና 2024 ተጧጡፎ ቀጥሏል
ከቀረበለት የሃሳብ ምርጫ በድምጹ ሊወስን ያለው እያንዳንዳንዱ ጋናዊ የትኛውን እንደሚመርጥ ውሳኔው የራሱ ይሆናልምስል NIPAH DENNIS/AFP

 

በእርግጥ ነው ፤ ሁለቱም ተቀናቃኝ ፓርቲዎች እንደሚያሸንፉ በሚተማመኑባቸው ጠንካራ ይዞታዎቻቸው ላይ ከማተኮር ይልቅ ለሁለቱም አማካይ በሆኑ አካባቢዎች ላይ ማተኮራቸው ነው የሚነገረው ። የምርጫ ቅስቀሳዎቻቸውም ሰላማዊ እንደሆነ ነው ሂደቱን በቅርብ የተመለከቱ ነዋሪዎች የገለጹት ።

የመዲናዋ የአክራ ከተማ ነዋሪው ክዋኩ አምፖንሳህ ለዶቼ እንዳሉት እስካሁን ካዩት እና ከታዘቡት የሁለቱም ፓርቲዎች የቅስቀሳ መልዕክቶች ምንም እንኳ ለእርሳቸው አሳማኝ ባይሆኑም  የምርጫዉን ሂደት ግን የሚያደናቅፍ ሆኖ አላገኙትም ።

የዛሚቢያ አና የጋና የዕዳ ቀውስ

"ሁለቱም የኤን.ፒ.ፒ እና የኤን.ዲ.ሲ ፓርቲዎች የገቧቸው የተስፋ ቃላት በታህሳስ ሰባቱ ምርጫ ላይ ውሳኔዬን በምንም መልኩ ሊነኩ አይችሉም። ምክንያቱም የገቡት ቃል  ተስፋ ሰጪ አይደለም ፤  በገቡት ቃል ውስጥ ምንም ተስፋ ሰጪ ነገር አላየሁም። በዘመቻቸው እስከ ዕለተ ምጽአት ድረስ ውሸታቸውን የሚቀጥሉ ነው የሚመስለኝ። »

ይህ የአምፖንሳህ ስጋት በእርግጥ መራጮች ከፖለቲከኞች ላይ እምነት ማጣታቸውን ማሳየቱን ነው ።

የባለፈው የጋና ምርጫ ገዢው የኤን ፒፒ ፓርቲ 275 መቀመጫዎችን ሲያሸንፍ ፤ በአንጻሩ ተቃዋሚው የኤን ዲ ሲ ፓርቲ የ137 መቀመጫዎችን አግኝተዋል። የተቀሩትን ወንበሮች ገለልተኞች ተቀራምተዋል።

የጋና ህገ መንግስት የፓርላማ አባላት ከወከሉት የፖለቲካ ፓርቲ ውጭ አልያም በገለልተኛነት እንዲወዳደሩ አይፈቅድም። ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን የፓርላማው አፈ ጉባኤ አልባን ባጊቢን አራት የምክር ቤቱን መቀመጫዎች ክፍት ማድረጋቸው ብርቱ ነቀፌታ ከማስነሳቱ ባሻገር ፖለቲካዊ አለመግባባት ማስከተሉን ነው መረጃዎች የሚያመለክቱት ።

የጋና የህክምና ባለሙያዎች ስደት

የአፈ ጉባኤው ውሳኔ ያስከተለው የፓርላማ ግርግር ምክር ቤቱ ላልተወሰነ ጊዜ ስራውን እንዲያቋርጥ ሁሉ አስገ,ድዶታል ። ይህ ደ,ግሞ ከሁለት ወራት በታች ጊዜ በቀረው አጠቃላዩ ምርጫ ላይ ተጽዕኖ እንዳያያሳድር ማስጋቱ አልቀ,ረም ። ምክንያቱም የህግ አ,ውጪው አካል አጠቃላይ እንቅስቃሴ ማስተጓጎሉ ምናልባትም በጀት እና ለምርጫው ወሳኝ የሆኑ ጉዳዮችን ከመወሰን በትንሹ ሊያዘ,ገይ የሚችልበት ዕድል መኖሩን አመላክቷል። የሆነ ሆኖ ግን ምክትሉ ፕሬዚዳንት ሊሆኑ ፨,አንድ ዙር ስልጣኑን ቀምሰው የተመለሱት ዳግመኛ ወደ መንበሩ ሊመለሱ አጓጊ ነገር ግን ብዙም እምነት ያላሳደሩ የቅስቀሳ ሃሳባቸውን ይዘው የምረጡኝ ዘመቻቸውን አጧጡፈዋል። አዲሱ የጎርጎርሳዉያን ዓመት 2025 ጋና ናና አኩፎ አዶን ሸኝታ አዲሱን ፕሬዚዳንት ትቀበላለች ።

ታምራት ዲንሳ

ማንተጋፍቶት ስለሺ