የገና ገበያ
ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 26 2009ማስታወቂያ
ስኳር ይጣፍጣል።ሲበዛ ግን፤ ሐኪሞች እንደሚሉት፤ በሽታ ያመጣል። አዲስ አበባ ግን ይጣፍጣትም፤ በሽታ ያምጣባት፤ ስኳር እንደ ሩቅ ዘመን ቁስ ትዝታ እየሆነባት ነዉ-ያዩ እንደሚሉት። የኦርቶዶክስተዋሕዶ ክርስቲያኖች የገና በዓል በመቃረቡ ነዉ መሰል ስኳር ቡታ ጋዝንም ከገበያ ለማስኮብለል ሳያደባ አልቀረም። ገና መጣ፤ አዲስ አበባ ላይ ስኳር የለም። ጋዝም «አለ» ማለት ያስቸግራል። አለም፤ የለምም ማለትም-የለም። በተለይ ነዳጅ ማደያ አጠገብ። ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ከአዲስ አበባ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ነጋሽ መሐመድ
ኂሩት መለሰ