የሁለቱ ጀነራሎች ስርዓተ ቀብር
ሐሙስ፣ ሰኔ 20 2011ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም የነበሩት የጀነራል ሰዓረ መኮንን እና የሜጀር ጀነራል ገዛኢ አበራ ሽኝት እና የቀብር ስነ ስርዓት ዛሬ መቀሌ ውስጥ ተካሂዷል። በስነ ስርዓቱ ላይ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል ባሰሙት ንግግር ኢትዮጵያ ከባድ ፈተና ላይ እንደሚትገኝ ገልጸው ሕገ መንግሥቱ እንዲከበር ጠይቀዋል። ሁለቱ ጀነራሎች ባለፈው ቅዳሜ በጀነራል ሰዓረ መኖሪያ ቤት በጠባቂያቸው ነበር የተገደሉት። የመቀሌው ዘጋቢያችን ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ ዘገባ አለው።
ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ