የጀርመን የቤተሰብ ፖሊሲ
ሐሙስ፣ የካቲት 26 2001ማስታወቂያ
ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ይህ ቁጥር ከአርባ ዓመት በኃላ በአስር ሚሊዮን ገደማ ቀንሶ ወደ ሰባ ሚሊዮን ማሽቆልቆሉ አይቀርም ። ይህም ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ እጅግ የከፋ የምጣኔ ሀብት ድክመት ውስጥ የምትገኘውን ጀርመንን ከሚያሳስቧት ጉዳዮች አንዱ ነው ። በአንዳንድ የአውሮፓ ሀገራት የሚወለዱ ህፃናት ቁጥር እየቀነሰ መሄድ አህጉሪቱን ከሚፈታተኗት አሳሳቢ ችግሮች አንዱ እና ምናልባትም ዋነኛው ሳይሆን አይቀርም ። የተወሰኑ አገራት የወሊድ መጠን ባለበት እንዲቀጥል በማድረግ የወደፊቱን አሳሳቢ ችግር ሲከላከሉ ችግሩ የሚያሰጋቸው አንዳንዶቹ ደግሞ ትኩረታቸውን ለውጥ ሊያመጡ ወደሚችሉ ዕርምጃዎች ላይ አድርገዋል ።