የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሳውዲ ጉብኝት
ሰኞ፣ ጥር 3 2002ማስታወቂያ
ሰፊ የምጣኔ-ሐብት ዘርፍ ልዑካንን አስከትለው ወደ አካባቢው የተጓዙት ቬስተርቬለ ቀደም ሲል ሳውዲት አረቢያን፣ ካታርንና የተባበሩ አረብ ኤሚሮችን ሲጎበኙ በሶሥቱም አገሮች ያካሄዱት ንግግር የሁለት ወገን የኤኮኖሚ ግንኙነትን ለማጠናከሩ ጉዳይ ዓቢይ ትኩረት የሰጠ ነበር። እርግጥ የመካከለኛው ምሥራቅ ውዝግብ፣ የኢራን አቶምና የአፍጋሃኒስታን ሁኔታ፤ እንዲሁም አል-ቃኢዳ በየመን የደቀነው አደጋም በሰፊው አነጋግሯል። ነቢዩ ሲራክ በቬስተርቬለ የሳውዲት አረቢያ ጉብኝት ላይ የላከው ዘገባ የሚከተለው ነው።
ነቢዩ ሲራክ
መስፍን መኮንን
አርያም ተክሌ