የጀርመን እርዳታ ለኢትዮጵያ
ማክሰኞ፣ ነሐሴ 10 2008ማስታወቂያ
የዓለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ገንዘቡ በኢትዮጵያ ለሚገኙ 600,000 ስደተኞች የምግብ ወጪ እና የገንዘብ ድጎማ የሚውል መሆኑን አስታውቋል። ስደተኞቹ ከኤርትራ፤ ደቡብ ሱዳን፤ ሱዳን እና ሶማሊያ የመጡ መሆናቸውንም ገልጧል። የጀርመኑ አምባሳደር ዮዓኺም ሽሚት ለስደተኞች ጉዳይ ጀርመን ከፍተኛ ፖለቲካዊ ትኩረት እንደምትሰጥ ጠቁመዋል። የዓለም የምግብ ድርጅት የኢትዮጵያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ጆን አይሌፍ ጀርመን ያደረገችው የገንዘብ ድጋፍ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ተናግረዋል።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
እሸቴ በቀለ
ሸዋዬ ለገሰ