1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን መራሔ መንግስት ጉብኝት በኢትዮጵያና ኬንያ

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 25 2015

ሾልስ ከኢትዮጵያ ፌደራዊ መንግስት፣ ከትግራይ ክልል ጊዚያዊ መሪዎችና ከአፍሪቃ ሕብረት ባለስልጣናት ጋር በሚያደርጉት ዉይይት የኢትዮጵያን የሰላም ስምምነት ገቢራዊነት፣የሰብአዊ ርዳታ አቅርቦትና የሱዳንን ጦርነት ትኩረት ሰጥተዉ ይነጋገራሉ

https://p.dw.com/p/4QqSQ
Berlin Präsident William Ruto Kenia und Kanzler Scholz
ምስል Kay Nietfeld/dpa/picture-alliance

ሾልስ አፍሪቃን ሲጎበኙ ያሁኑ ሁለተኛቸዉ ነዉ

የጀርመን መራሔ መንግስት ኦላፍ ሾልስ በኢትዮጵያና በኬንያ የሚያደርጉትን የሶስት ቀናት ጉብኝት ነገ ከአዲስ አበባ ይጀምራሉ።ሾልስ ከኢትዮጵያ ፌደራዊ መንግስት፣ ከትግራይ ክልል ጊዚያዊ መሪዎችና ከአፍሪቃ ሕብረት ባለስልጣናት ጋር በሚያደርጉት ዉይይት የኢትዮጵያን የሰላም ስምምነት ገቢራዊነት፣የሰብአዊ ርዳታ አቅርቦትና የሱዳንን ጦርነት ትኩረት ሰጥተዉ ይነጋገራሉ።የጀርመን የኩባንያና የንግድ ድርጅት ተወካዮችን የሚያስከትሉት ሾልስ ከኬንያ መሪዎችና ባለሐብቶች ጋር ሥለሁለቱ ሐገራት የንግድ ልዉዉጥና የተፈጥሮ ጥበቃ ይመክራሉ።ከአፍሪቃ ትልቁን የእንፏሎት ወይም የጆኦተርማል ኃይል ማመንጫ ተቋምን ይጎበኛሉም።

ፊሊፕ ዛንድነር

ይልማ ኃይለሚካኤል 

ነጋሽ መሐመድ

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር