የጀርመንና የአፍሪቃ ትብብር፣
ረቡዕ፣ ሚያዝያ 21 2001ማስታወቂያ
ሚንስትር ደኤታ ፔተር አሞን ዛሬ አዲስ አበባ ዉስጥ ለአፍሪቃ ሕብረት አባል ሐገራት አምባሳደሮች እንደተናገሩት መንግሥታቸዉ በአፍሪቃ ሠላም ለማስፈን በሚደረገዉ ሁለንታዊ ጥረትን ለመደገፍ ተጨባጭ’ እርምጃዎችን እየወሰደ ነዉ።ሚንስትር ደ-ኤታዉ አዲስ አበባ የገቡት በተለያዩ የአፍሪቃ ሐገራት የሚሰሩ ሠላሳ አምስት የጀርመን አምባሳደሮችን አስከትለዉ ነዉ።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ታደሰ እንግዳዉ እንደዘገበዉ ፔተር አሞን ጀርመን ለአፍሪቃ ሕብረት የሠላምና የፀጥታ ምክር ቤት በሃያ-ሚሊዮን ዮሮ የምታሰራዉን ሕንፃ ቅርፅ ዛሬ መርቀዉ ከፍተዋልም።--ታደሰ እንግዳው፣
ነጋሽ መሐመድ፣
ተክሌ የኋላ፣