የጀልባ ስደተኞችና የኢጣልያ ፖሊስ
ሐሙስ፣ ሚያዝያ 6 2003ማስታወቂያ
በትናንትናው ዕለትም ከላምፔዱዛ በሰተሰሜን ምዕራብ በምትገኘው በፓንቴሌሪያ ደሴት አቅራቢያ ሁለት ስደተኞች ጀልባ ውስጥ ሞተው ተገኝተዋል ። ከዚሁ አካባቢ ወደ 250 የሚሆኑ በጀልባ በመጓዝ ላይ የነበሩ ስደተኞች የኢጣልያ ድንበር ጠባቂ መርከብ ደርሰውላቸው ከመስጠም ተርፈዋል ። ስደተኞችን የጫኑ ጀልባዎችን የመፈለጉ ሃላፊነት የኢጣልያ የፊናንስ ፖሊስ አውሮፕላን አብራሪዎች ነው ። ጀልባዎቹ ያሉበትን አቅጣጫ መጠቆም እና የአደጋ ደራሽ ሰራተኞችን ወደ ስፍራው መምራት የአብራሪዎቹ ተግባር ነው ።
ሽቴፋን ትሮንደለ
ሂሩት መለሰ