የዶክተር መረራ የዋስትና ጥያቄ
ዓርብ፣ መጋቢት 1 2009ማስታወቂያ
ዛሬ ያስቻለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19 ነኛ ወንጀል ችሎት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር ዶክተር መረራ ጉዲና ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ ሳይቀበለው ቀርቷል። ዶክተር መረራ ከጤንነታቸው አንጻር ቤተሰቦቻቸው በቅርበት እንዲከታተሉዋቸው ከማዕከላዊ ማረሚያ ቤት ወደ ቃሊቲ እንዲዛወሩ ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቷል። ዶክተር መረራ በውሳኔው እጅግ ማዘናቸውን ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል። ችሎቱን የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዝርዝሩን ልኮልናል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ