የዶክተር መረራ ከእስር መፈታት
ረቡዕ፣ ጥር 9 2010ማስታወቂያ
የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ፣ኦፌኮ፣ ሊቀመንበር ዶክተር መረራ ጉዲና ከአንድ ዓመት በላይ እስር ላይ ከቆዩ በኋላ ዛሬ እቤታቸዉ እንደደረሱ በሰጡት መግለጫ በመፈታታቸዉ ቢደሰቱም የሌሎች መታሰር እንዳላስደሰታቸዉ እና እንደሚያሳስባቸው ተናግረዋል። ዶክተር መረራ ወደ መኖርያ ቤታቸዉ ከገቡ በኋላ ለህዝቡና ለፓርቲያቸዉ መልክት አስተላልፈዋል።
የኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙላቱ ተሾመ ዶክተር መረራ መፈታታቸዉ «እንደ ፓርቲ የኦሮሞ ትግል ዉጤት ነዉ» ስሉ ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል። የፓርቲዉ መሪ ዶክተር መረራ ቢፈቱም፣ አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ ወደ 500 የሚጠጉ የፓርቲው አባላት አሁንም በእስር ላይ እንደiሚገኙም አቶ ሙላቱ ገልጸዋል።
ባለፈዉ ሰኞ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አቶ ጌታቸው አምባዬ የፍርድ ሂደታቸው በመታየት ላይ የሚገኙ ከ528 ተጠርጣሪዎ ክሳቸዉ ተቋርጦ እንደሚለቀቁ አስታዉቀዉ ነበር። በዚህም መሰረት ፣ ዶክተር መረራ ጨምሮ በፌዴራል ደረጃ 115 እስረኞች ዛሬ ተለቀዋል።
መርጋ ዮናስ
ነጋሽ መሀመድ