የዶቸ ቬለ እግር ኳስ ተጫዋች -ጆኒ ግደይ
ዓርብ፣ ሰኔ 29 2004ማስታወቂያ
ጆኒ ግደይ ለዶቸ ቬለ እግር ኳስ ቡድን ይጫወታል።ቡድኑ በተመሳሳይ ደረጃ ላይ ካሉ የከተሞችና የትላልቅ መስሪያ ቤት ቡድኖች ጋ ይጋጠማል። ወጣቱ የዶቸ ቬለ የእግር ኳስ ቡድንን ከመቀላቀሉ በፊት ለትልቁ የጀርመን ፖስታ ቤት DHL ቡድን ይጫወት ነበር። ለምን ወደ ዶቸ ቬለ ቡድን እንደቀየረ አጫውቶናል።
ለጀርመን ብሔራዊ ቡድን የሚጫወቱ በርካታ የውጭ አገር ዜጋ ተወላጆች አሉ። ይሁን እና አብዛኞቹ ከአውሮፓ ናቸው። የሌሎቹንም የአውሮፓ ቡድን ብንወስድ እንደዚሁ።
በቡድናቸው ብዙ የአፍሪቃ ተወላጆች አይታዩም። ከምን የመጣ ነው?አስተያየቱን ጠይቀነዋል።
ብዙ እግር ኳስ ተጫዋቾች ባሉበት አገር ተዋቂ ሆኖ የመውጣቱ እድል ጠባብ ነው ይላል ጆኒ። አንድ ቡድን አንድን ተጫዋች እንዲወስደው ምን ዓይነት ነገሮች መሟላት አለባቸው? ጆኒ ስለ ኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተስፋም ያካፈለን አለ። ሙሉውን ዝግጅት ማድመጥ ይቻላል።
ልደት አበበ
ሒሩት መለሰ