የኢንዱስትሪ መንደር ግንባታ በድሬዳዋ
ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 6 2009ማስታወቂያ
የድሬዳዋ ከተማን የኢንዱስትሪ የኢንቬስትመንት እና የአገልግሎት ማዕከል ለማድረግ ልዩ ልዩ ጥረቶች በመደረግ ላይ መሆናቸውን የከተማዋ አስተዳደር አስታወቀ ። በዚሁ መሠረት በድሬዳዋ በ4ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የኢንዱስትሪ ፓርክ ለመገንባት የተጀመረው ሥራ ከጥረቶቹ አንዱ ነው ። ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር እንደዘገበው በከተማዋ ለመጀመሪያው ዙር የኢንዱስትሪ መንደር ግንባታ የሚውል የ150 ሄክታር መሬት ርክክብ ተካሂደል ። ግንባታው በ9 ወር ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ