የይርጋለም ከተማ ወጣት መምህራን
ዓርብ፣ ጥር 1 2007ማስታወቂያ
መምህርት ሰብለ ሽፈራው እና መምህር ታምራት ታደሰ ይባላሉ። ወጣት መምህራኑ እንደሚሉት አስተማሪ መሆን ሁሌም ምኞቻቸው ነበር።ታምራት የ9ኛ ክፍል የእንግሊዘኛ ቋንቋ መምህር ነው። ወደ ይርጋለም የሄደው በዚሁ በሥራ እድል ምክንያት ነው፤ ያደገው ግን ሐዋሳ ከተማ ነው። መምህርት ሰብለም እንዲሁ ከይርጋለም ከተማ 12 ኪሎ ሜትር ወጣ ብሎ በሚገኘው ትምህርት ቤት ውስጥ የ10ኛ ክፍል የባዮሎጂ መምህርት ናት።ወጣት መምህራኑ፤ ከከተማ ትንሽ ወጣ ብሎ ማስተማሩን እንደ ህዝባዊ ግዴታ ነው የሚቆጥሩት። በዚህም ደስተኛ ናቸው።
መምህራኑ ከሙያው የሚወዱት ነገር ምንድን ነው? አስተማሪነትስ ምን አይነት ኃላፊነት አለው? በመምህርነት ከሚያገለግሉት ሁለት ወጣት መምህራን ጋር በወጣቶች ዓለም ዝግጅት ያካፈሉንን ከዚህ በታች በድምፅ ያገኛሉ።
ልደት አበበ
ሂሩት መለሰ