1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዩጋንዳ ምርጫ እና ስጋቱ

ረቡዕ፣ ጥር 5 2013

ዩጋንዳ ዉስጥ ነገ የሚደረገዉን ፕሬዝደንታዊና የምክር ቤት አባላት ምርጫ ለመታዘብ ጥያቄ ያቀረቡ መንግስታትና ድርጅቶች የታዛቢነት ፈቃድ መከልከላቸዉን አስታወቁ።

https://p.dw.com/p/3nsaW
Uganda Kampala | Präsidentschaftswahl: Wahlplakate
ምስል Sumy Sadurni/AFP/Getty Images

ዩጋንዳ ዉስጥ ነገ የሚደረገዉን ፕሬዝደንታዊና የምክር ቤት አባላት ምርጫ ለመታዘብ ጥያቄ ያቀረቡ መንግስታትና ድርጅቶች የታዛቢነት ፈቃድ መከልከላቸዉን አስታወቁ። የዩጋንዳ የሲቢል ማሕበረሰብ ጥምረት፣ ዩናይትድ ስቴትስና የአዉሮጳ ሕብረት በየፊናቸዉ እንዳሉት ምርጫዉን ለመታዘብ ያቀረቡትን ጥያቄ የዩጋንዳ አስመራጭ ኮሚሽን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ዉድቅ አድርጎታል።በካምፓላ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ እንዳስታወቀዉ ምርጫዉን ለመታዘብ ፍቃድ ከጠየቀላቸዉ አሜሪካዉን ፍቃድ ያገኙት 15ቱ ብቻ ናቸዉ።በዚሕም ምክንያት ዩናይትድ ስቴትስ ምርጫዉን እንደማትታዘብ ኤምባሲዉ አስታዉቋል።የአዉሮጳ ሕብረት እንዳስታወቀዉ የምርጫ ባለሙያዎቹ እስከ ዛሬ ፈቃድ አላገኙም።እዚያዉ ዩጋንዳ የሚገኘዉ አንድ የሲቢል ማሕበራት ጥምረት እንደሚለዉ ደግሞ ለ1900 ታዛቢዎች ፈቃድ ጠይቆ የተሰጠዉ ለ10ሩ ብቻ ነዉ። 

 

ነጋሽ መሐመድ 

አዜብ ታደሰ