የዩናይትድ ስቴት ጦር በአፍሪቃ
ዓርብ፣ ሰኔ 10 2008ማስታወቂያ
ዩናይትድ ስቴትስ አፍሪቃ ዉስጥ ያሰፈረችዉ ጦር፤ ለአፍሪቃ ወታደሮች የምትሰጠዉ ሥልጠና እና የምታስታጥቀዉ ጦር መሳሪያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነዉ።የሠፈረዉ ጦር ቁጥር መጨመርም ሆነ ወታደራዊ ሥልጠናዉና የጦር መሳሪያዉ መብዛት አፍሪቃ ዉስጥ የሚከሰቱ ግጭቶችና የአሸባሪዎችን ጥቃት ለመከላከል የፈየደዉ የለም የሚሉ አሉ።የአሜሪካ ባለሥልጣናት ግን ለአፍሪቃ የሚሰጡት ወታደራዊ ድጋፍ ኢቦላን የመሳሰሉ ተዛማች በሽታዎችን ለመከላከል ሳይቀር ብዙ ጠቅሟል ባይ ናቸዉ።ዩናይትድ ስቴትስ አፍሪቃ ዉስጥ ከሁለት ሺሕ በላይ ወታደሮች አስፍራለች።የሰላዩ ቁጥር በግልፅ አይታወቅም።የዋሽግተን ዲሲዉ ወኪላችን መክብብ ሸዋ ተከታዮን ዘገባ ልኮልናል።
መክብብ ሸዋ
ነጋሽ መሐመድ