የአሜሪካን ምክር ቤት አባላት ጉብኝት
ሐሙስ፣ ነሐሴ 17 2010ማስታወቂያ
የዩናይትድ ስቴትስ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ኢትዮጵያን እየጎበኙ ነው። እንደራሴዎቹ 5 ናቸው። ከመካከላቸው በኢትዮጵያ የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታውን የሚያፋጥኑ ተግባራት እንዲከናወኑ እና ሰብዓዊ መብቶችም እንዲከበሩ ጥሪ የሚያስተላልፈውን ኤች አር 128 የተባለውን ህግ ያረቀቁ እና እንዲጸድቅ ጥረት ያደረጉት ኮንግረስማን ክሪስ ስሚዝ ይገኙበታል። የልዑካን ቡድኑ ዓላማ የኢትዮጵያ እና የዩናይትድ ስቴትስን ጥቅም ያገናዘበ ነው ሲሉ በዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪቃ ጉዳይ ቃል አቀባይ ለዶቼቬለ ተናግረዋል።
መክብብ ሸዋ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ