የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የፍርድ ቤት ውሎ
ረቡዕ፣ ሰኔ 15 2008ማስታወቂያ
የካቲት 29፣ 2008 ዓም በአዲስ አበባው የአሜሪካን ኤምባሲ በር ላይ ያልተፈቀደ ሰልፍ በማካሄድ ደንብ ጥሳችኋል ተብለው በተከሰሱ 22 የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ዛሬ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቅ የነበረው ብይን ለሌላ ጊዜ ተላለፈ ። ዛሬ የተሰየመው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መናገሻ ምድብ ችሎት በተማሪዎቹ ጉዳይ ላይ ብይን ለመስጠት ሌላ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል ። ችሎቱ ተከሳሾቹ ያቀረቡትን ንብረታቸውን የመረከብ አቤቱታም ተቀብሎ ትእዛዝ ሰጥቷል ። ስለ ዛሬው ችሎት የተማሪዎቹን ጠበቃ ያነጋገረው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚዘብሔር ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚዘብሔር
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ