1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዛላንበሳ ድንበር ለማለፍ የይለፍ ፈቃድ መጠየቁ

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 17 2011

በኢትዮጵያ ድንበር ከተማ ዛላምበሳ በኩል ወደ ኤርትራ በመጓዝ ላይ የነበሩ ኢትዮጵያውያን «የይለፍ ፍቃድ የላችሁም» በሚል ወደ ኤርትራ እንዳይገቡ በሀገሪቱ መንግሥት ወታደሮች መከልከላቸው ተገለፀ። እገዳው በኤርትራ በኩል ከዛሬ ጠዋት 12 ሰዓት ጀምሮ መተግበር መጀመሩን የዛላምበሳ ከተማ ነዎሪዎች ለDW ገልፀዋል

https://p.dw.com/p/3Aejo
Karte Äthiopien Eritrea Grenze Englisch

በርካታ ተሽከርካሪዎች ድንበር ላይ መሆናቸው ተገልጿል

የኢትዮጵያ እና ኤርትራ መንግሥታት በደረሱት ስምምነት መሠረት ባሳለፍነው መስከረም ወር ድንበሮቻቸውን ከፍተው የሁለቱ ሃገራት ህዝቦች ለተለያዩ ተግባራት ድንበር አቋርጠው ሲመላለሱ ቆይተዋል፡፡ እስካሁን በነበረውም በኢትዮጵያ ይሁን በኤርትራ በኩል የይለፍ ፍቃድ ሲጠየቅ እንዳልነበረ የመቀሌው ዘጋቢያችን ያነጋገራቸው የዛላምበሳ ነዎሪዎች እና ተጓዦች ይገልፃሉ፡፡ በዛሬው ዕለት በኤርትራ በኩል የይለፍ ፍቃድ በመጠየቁ በርከት ያሉ መኪኖች በድንበሩ አቅራቢያ ቆመው እንደሚገኙ በትግራይ ምሥራቃዊ ዞን የጉለመከዳ ኮምኒኬሽን ፅሕፈት ቤት የፕሬስ ባለሙያ አቶ የዕብዮ ሙልጌታ ለDW ተናግረዋል፡፡ ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ ዝርዝሩን ልኮልናል።

ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ