የዙሪክ ዳይመንድ ሊግ እና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች
ዓርብ፣ ነሐሴ 24 2011ማስታወቂያ
በተለይ የ5000 ሜትር ውድድሩ ድል ከኢትዮጵያውያ አትሌቶችም እጅ እንደማይወጣ ቢገመትም በውድድሩ ወቅት ተፈጠረ ባሉት መዘናጋት በበዩጋንዳዊው አትሌት ተቀድመው 50ሺ ዶላርና ልዩ ሽልማት አምልጧቸዋል። በውድድሩ አትሌት ሀጎስ ገብረ ሕይወት በሁለተኛነት ሲያጠናቅቅ ጥላሁን ኃይሌ አራተኛ ፤ ሰለሞን በረጋ ደግሞ አምስትኛ ደረጃ አግኝተዋል። አትሌቶቹ የዙሪኩ ስህተት በኳታር አስተናጋጂነት በሚካሂደው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ እንዳይደገም ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚወስዱም ከውድድራቸው በኋላ ለዶቼ ቬለ DW ተናግረዋል። በሴቶች በተካሂደው የ1500 ሜትር ፍፃሜ ውድድር አትሌት ገንዘቤ ዲባባ የአራተኛነትን ደረጃ አግኝታለች። በስፍራው ተገኝታ ውድድሩን የተከታተለችው ሃይማኖት ጥሩነህ ዝርዝሩን ልካልናለች።
ሃይማኖት ጥሩነህ
ሸዋዬ ለገሠ
ተስፋለም ወልደየስ