የዓለም የምግብ ቀንና ስጋት7 ጥቅምት 2001ዓርብ፣ ጥቅምት 7 2001በዓለም በምግብ ማጣትና እጥረት እየተቸገሩ የሚገኙ በርካታ ወገኖች ባሉበት በዚህ ወቅት የበለፀጉት አገራት እነሱን ለመርዳት ከመፋጠን ይልቅ ትኩረታቸዉ በባንኮች ላይ የተከሰተዉ የፋይናንስ ቀዉስ ላይ ሆኗል ሲሉ የቀድሞዉ የተመድ ዋና ጸሐፊ ኮፊ አናን ወቀሱ።https://p.dw.com/p/FbS510,000 የሚሆኑ ህፃናት በድሃዎቹ አገራት የረባ ምግብ በማጣት ይሞታሉምስል APማስታወቂያ እሳቸዉ እንደሚሉት በሶስተኛዉ ዓለም አገራት 10,000 ህፃናት በዛሬዋ ዕለት ብቻ የተመጣጠነ ምግብ በማጣት ህይወታቸዉ ያልፋል። የዓለም የረሃብ ሁኔታን የሚያሳየዉ መዘርዝር በመኩሉ በዓለማችን ከሚገኙት አገራት 33ቱ በከፋ የርሃብ ችግር ላይ እንደሚገኙ ይፋ አድርጓል።