የዓለም እግር ኳስ ግጥምያ ውድድር ምድብ
ቅዳሜ፣ ኅዳር 26 2002ማስታወቂያ
በዕጣው መሠረት ጆሃንስበርግ ላይ ሰኔ 4 ቀን. ውድድሩን የሚከፍቱት ደቡብ አፍሪቃና ሜክሢኮ ይሆናሉ። የቀድሞው የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዚደንት ኔልሰን ማንዴላ አገራቸው ለአስተናጋጅነት በመብቃቷ የተሰማቸውን ደስታ ሲገልጹ የወቅቱ ፕሬዚደንት ጄኮብ ዙማ ደግሞ ከስድሥቱ ተሳታፊ የአፍሪቃ አገሮች አንዱ የዋንጫ ባለቤት እንደሚሆን ተንብየዋል። የዕጣ አወጣጡ ሥነ-ሥርዓት በሙዚቃ፣ በዳንኪራና የደቡብ አፍሪቃን ውበት በሚያሳዩ የቪዲዮ ፊልሞች ሲታጀብ ኦስካር ተሸላሚዋ የሆሊዉድ ተዋናይ ቻርሊዝ ቴሮን፣ የቀድሞው የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን አምበል ዴቪድ ቤክሃም፣ ሃይሌ ገብረ-ሥላሴና ሁለት የደቡብ አፍሪቃ ስፖርተኞች በተለይ የምሽቱ ከዋክብት ነበሩ። ከስምንቱ ምድቦች መካከል ብራዚል የምትገኝበት ምድብ-ሰባት በጥንካሬው ከወዲሁ የሞት ምድብ የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል። የብራዚል ተጋጣሚ ሆነው የተደለደሉት አገሮች ሰሜን ኮሪያ፣ አይቮሪ ኮስትና ፖርቱጋል ናቸው።
አዜብ ታደሰ