የዓለም እግር ኳስ ውድድር ፍጻሜ
ሰኞ፣ ሐምሌ 5 2002ማስታወቂያ
ስፓኝ የመጀመሪያ ለሆነው የዓለም ዋንጫ ድሏ የበቃችው ኔዘርላንድን በተጨማሪ ሰዓት ውስጥ 1-0 በመርታት ነው። የዝግጅቱ ስኬት የአገሪቱን የመስተንግዶ ብቃት አጠያያቂ ሲያደርጉ የቆዩትን ተጠራጣሪዎች ሁሉ ጸጥ ሲያሰኝ ሂደቱ ደቡብ አፍሪቃን ብቻ ሣይሆን መላውን የአፍሪቃ ክፍለ-ዓለም ነው ያኮራው። የ 92 ዓመቱ አንጋፋ የደቡብ አፍሪቃ የነጻነት መሪ ኔልሰን ማንዴላም ባለፈው ምሽት በጆሃንስበርጉ ሶከር-ሢቲይ ስታዲዮም በአካል መገኘታቸው መዝጊያውን ስነ-ስርዓት የበለጠ ክብር አጎናጽፎታል። የዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ውድድር የእግር ኳስ ጥበብ በጉልበት የአጨዋወት ዘይቤ ላይ፤ የቡድን አጨዋወትም በግለሰብ ተውኔት ላይ አይለው የታዩት ነበር።