የዓለም አቀፍ የጦር መሣሪያ ወጪ መቀነስ7 ሚያዝያ 2006ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 7 2006በዓለም ደረጃ በአጠቃላይ ለጦር መሣሪያ ግዢ የሚወጣው ገንዘብ ከበፊቱ ጋር ሲነፃፀር በትንሹ ዝቅ ብሏል። ይህም የሆነበት ምክንያት ትናንት ስቶኮልም ላይ ይፋ የወጣው አንድ ጥናት እንደሚያመላክተው ዮናይትድ ስቴትስ ለኢራቅ ጦርነት የምታወጣው ገንዘብ በመቀነሱ ነው።https://p.dw.com/p/1BiP3ምስል picture-alliance/dpaማስታወቂያ በአንፃሩ በሌሎች አካባቢዎች ለመሣሪያ ግዢ ገንዘብ ይፈሳል። ይህን ያለው መቀመጫውን ስቶኮልም - ስዊዲን ያደረገው በምሕፃሩ « ሲፕሪ» በመባል የሚታወቀው አለም አቀፍ የሰላም ምርምር ተቋም ነው። የዶይቸ ቬለዋ ሄለ ጄፕሰንን ዘገባ የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል እንደሚከተለው አጠናቅሮታል። ሄለ ጄፕሰን/ ይልማ ኃይለ ሚካኤል አርያም ተክሌ