የዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር መግለጫ
ሐሙስ፣ መጋቢት 15 2014ማስታወቂያ
የዩናይትድ ስቴትስ ሕግ መምሪያና መወሰኛ ምክር ቤቶች ያረቀቋቸዉ ኢትዮጵያን የሚመለከቱ ሁለት ሕግጋትን የኢትዮጵያ መንግሥት አጥብቆ እንደሚቃወማቸዉ በአፍሪቃ ቀንድ ለዩናይትድ ስቴትስ ልዩ መልዕክተኛ መናገሩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ።የሚኒስቴሩ ቃል ዐቀባይ ዲና ሙፍቲ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ "የዳቦ ስም የተሰጣቸው" ያሏቸው ረቂቅ ሕግጋት የኢትዮጵያ መንግሥት ደካማና የሚጠመዘዝ መንግሥት እንዲሆን የሚያደርጉ ናቸው ብለዋል።HR6600 እና S.3199 የተባሉት ረቂቅ ሕግጋት ከፀደቁ የሁለቱን ሐገራት ታሪካዊ ግንኙነት ክፉኛ ይጎዳሉ ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ለልዩ መልእክተኛው መናገራቸው አምባሳደር ዲና አስታዉቀዋል።
ሰለሞን ሙጬ
ነጋሽ መሐመድ
አዜብ ታደሰ