የወጣቶች መድረክ
ዓርብ፣ ታኅሣሥ 26 2011ማስታወቂያ
አበበ ፈንታሁን ይባላል፡፡በተለያዩ ምክንያቶች ወላጆቻቸው ያጡና ተጥለው የተገኙ ህፃናትን በመንከባከብ ይታወቃል፡፡ ከ2001 ዓ.ም ጀምሮ 'ሎላ' የተሰኘ የህፃናት ማሳደግያ ድርጅት ከፍቶ በርከት ያሉ ወላጅ አልባ ህፃናት እያሳደገ ነው፡፡ አበበ ራሱ በህፃንነት ጊዜው ጎዳና ተጥሎ ከባድ ሕይወት ማሳለፉ ይናገራል፡፡ በአሁኑ ግዜ መቐለ በሚገኘው 'ሎላ የህፃናት ማእከል' 21 ወላጆቻቸው ያጡ ህፃናት እየተንከባከበ ነው፡፡ ሌሎች ከ70 በላይ ህፃናትም ከወላጆቻቸው ጋር ሆነው በአበበ ፈንታሁን ድርጅት ይረዳሉ፡፡
ሚሊዮን ኃይለ ስላሴ
ማንተጋፍቶት ስለሺ