የኮንትራት ሰራተኞችን በህጋዊ መንገድ ለመላክ የተያዘው እቅድ
እሑድ፣ ጥር 17 2007ማስታወቂያ
በተለያዩ መንገዶች ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ሃገራት ለሥራ የሚሄዱ ኢትዮጵያውን ልዩ ልዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንደሚፈፀምባቸው ተደጋግሞ ሲነሳ ቆይቷል ። ከ 1 ዓመት በፊት ደግሞ የሳውዲ መንግሥት ህገዊ አይደሉም ሲል ያባረራቸው ከ160 ሺህ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን አብዛኛዎቹ ባዶ እጃቸውን ወደ ሃገራቸው ተመልሰዋል ። በርካቶች አሁንም በሳውዲ አረቢያ ና በሌሎችም የመካከለኛው ምሥራቅ ሃገራት እንደሚንገላቱ ይሰማል ። እነዚህ ችግሮች አሁንም እንዳልተወገዱ በሚሰማበት በዚህ ወቅት ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት የኮንትራት ሠራተኞችን በህጋዊ መንገድ ወደ ውጭ ለመላክ ዝግጅቱን እያጠናቀቀ መሆኑን አስታውቋል ። ይህን ለማሳካትም መንግሥት የዜጎችን መብትና ክብር የሚያስጠብቅ ያለውን አዲስ ህግ ማርቀቁን ብዙ ኢትዮጵያውያን ለሥራ ከሚሄዱባቸው ሃገራት መንግሥታት ጋር የሥራ ስምምነቶችን ለመፈራረም ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገልጿል ። የእንወያይ ዝግጅት የኮንትራት ሠራተኞችን ወደ ውጭ ሃገራት በህጋዊ መንገድ ለመላክ የተያዘው እቅድ ላይ ያተኩራል ።
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ