የኮቪድ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ
ረቡዕ፣ ሰኔ 1 2014ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ ዉስጥ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ እንዳዲስ ማገርሸቱን የሐገሪቱ የጤና ሚኒስቴር እና የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እየገለጹ ነው፡፡ በኮሮና ተሕዋሲ የተያዙ ሰዎች የሚታከሙበት የየካ ኮተቤ ሆስፒታልም በህሙማን ብዛት መጨናነነቁን አሳዉቋል።የሆስፒታሉ ዋና ዳሬክተር ዶ/ር ያሬድ አግደው ለዶይቼ ቬለ እንደገለጹት ከሶስት ሳምንታት በፊት ሆስፒታሉ ዉስጥ አንድም የኮቪድ ህሙም አልነበረም።ባለፉት 10 ቀናት ግን ወደ ሆስፒታሉ ከገቡ ከ80 በላይ ሰዎች እስከ ሞት የሚያደርስ ሁኔታ ላይ ያሉ ይገኛሉ ብለዋል፡፡
ስዩም ጌቱ
ነጋሽ መሐመድ
ኂሩት መለሰ